Amharic: The Uluru Statement from the Heart

Uluru Statement from the Heart

Uluru Statement from the Heart Source: Jimmy Widders Hunt

በግንቦት ወር 2017 አም የአቦርጅናል እና ቶረስ ስትሬት አይላንደር ተወካዮች በአንድ ላይ በመሆን በመጀመሪያው ብሄራዊ ህገ መንግስት ስምምነት ዙሪያ በኡሉሩ አቅራቢያ ተሰባስበን የኡሉሩን መግለጫ ከልባችን በማፍለቅ ለአውስትራሊያ ህዝብ አቅርበናል። መግለጫው የመጀመሪያዎቹ ዜጎች በህገ-መንስቱ እንዲካተት ለፓርላምው ድምጻቸው ያሰሙበት ፤ እንዲሁም እውነትን በመናገር ላይ የተመሰረተ ስምምነት (ውል ) ላይ ለመደረስ ይመሩበት ሂደት ነው ። ይህ ከአውስትራሊያ ቀደምት ዜጎች ጋር በአገር አቀፍ ደረጃ በየክልሉ ተደርገው ከነብሩት 13 ውይይቶች ማጠቃለያ የተገኘ ውጤት ነው ። መግለጫውም በአውስትራሊያ ቀደምት ዜጎች እና የአውስትራሊ ዜጎች ማካከል በእውነት ፤ በፍትህ እና የራስን መብት በራስ መወሰን ላይ ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን ለመመስረት የሚሻ ነው ። ሙዚቃ ፍራንክ ያማ ፤ፎቶግራፍ ፡ ጂሚ ዊደርስ ሃንት ።


ይህ የሆነውም ሁለት አመትን የፈጀን ክርክርር እና ውይይትን  ተከተሎ ሲሆን የተነደፈው እና የተመራውም በ13 የመጀመሪያዎቹ ብሄሮች ክልላዊ ውይይቶች  ላይ ሲሆን ፤ በ250  የአቦርጅናል እና ቶረስ ስትሬት አይላንደር ተወካዮችም ተቀባይነትን አግኝቷል ፡፡ይህንም በአውስትራሊያ ነባር ዜጎችና ነባር ዜጎች ባልሆኑት በሁሉም አውስትራሊያውን መካከል ግንኙነትን መመስረት የሚጠይቅ ሲሆን መሰረቱንም የሚያደርገው በእውነት ፤ ፍትህ እና የራስን መብት በራስ መወሰን የሚሉትን በማክበር ፤እንዲሁም ሉዓላዊነት ከድርድር ውስጥ ሳያስገቡ ለዕርቅ ወደፊት  መጓዝ የሚለውን ያጠቃልላል፡፡

በ2017 አም በብሄራዊ ህገ መንግስት ስምምነት ዙሪያ በአንድ ላይ በመሆን በደቡባማው ሰማይ ዙሪያ ተሰባስበን ፤ ያሉትንን አጠቃላይ ነጥቦች በአንድነት በማድረግ ይህን ልባዊ የሆነ መግለጫ አውጥተናል ፡፡የእኛ የሆኑት የአቦርጅናል እና ቶረስ ስትሬት አይላንደር ጎሳዎች የአውስትራሊያ አህጉር የመጀመሪያዎቹ ሉአላዊ ሕዝብ ሲሆኑ ፤ በአጠገብ ያሉ ደሴቶችም በራሳችን ህግ እና ልማዶች የሚመሩ ናቸው ፡፡ ይህንንም የሰሩት ቅድመ አያቶቻችን ናቸው፡፡

ይህም በባህላችን እማኝነት  ፤ ከፈጣሪ  ፤ በተለምዶአዊ ህግ  ‘ ጊዜ የማይሽረው ’ ከሳይንስ አንጻርም ከ60,000 አመት በፊት የተሰራ ነው ፡፡ ይህ ሉአላዊነት መንፈሳዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ የአባቶቻችን ከመሬት ወይም ‘ ከተፈጥሮ ‘ ጋር ያላቸው ትስስር ነው ፡፡  አቦርጅናል እና ቶረስ ስትሬት አይላንደር ህዝቦች በዚያ የተውለዱት ፤  ከዚያ ጋር ተቆራኝተው አሉ ፤ ወደፊትም አንድ ቀን በእዚያው ከቅድመ አያቶቻችን ጋር ይዋሃዳሉ ፡፡ግንኙነቱም የተመሰረተው በባለቤትነት እና በአፈር  ፤ ወይም በሉአላዊነት ላይ ነው ፡፡

በምንም ጊዜ ቢሆን ያልተተው እና ከዘውድ ሉአላዊነት ጋር አብሮ የኖረ ነው ፡፡አለበለዚያ እንዴት ሊሆን ይችላል ? እነዚያ ህዝቦች ለስልሳ  ሺህ አመታት መሬታቸውን ቀምተው የተቀደሰውን ትስስራቸን ከአለም ታሪክ እንዲጠፋ ያደረጉት ላለፉት ሁለት መቶ አመታት ብቻ ነውን ? ፤ የቀደመው ሉአላዊነት ተጨባጭ በሆነ ህገ መንግስታዊ ለውጥ እና መዋቅራዊ ማሻሻያ በመላው አውስትራሊያ እንደገና እንደሚጎመራ እናምናለን ፡፡

በቁጥር በምድራችን ላይ ካሉት ሰዎች በላይ እኛ በእስር ላይ እንገኛለን ፡፡እኛ በተፈጥሮ ወንጀለኛ ህዝብ አይደለንም ፡፡ታይቶ በማይታወቅ መጠን ልጆቻችን ከወላጆቻቸው ተለይተዋል ፡፡ይህ የሆነው እኛ ለእነሱ ፍቅር ስለሌለን አይደለም ፡፡ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ወጣቶች በእስር ቤቶች እንግልትን ያሳልፋሉ፡፡ለወደፊቱ ተስፋችን ሊሆኑን ይገባል ፡፡ያለንበት ቀውስ በግልጽ የሚነግረን የችግራችን ምንጭ ከመዋቅሩ መሆኑን ነው ፡፡

ይህ አቅም ከማጣት ሳቢያ የምናየው ስቃይ ነው ፡፡ህገ መግስታዊ ማሻሻያን እንፈልጋለን ፤ ህዝባችንንም በማብቃት በአገራቸው ትክክለኛውን ቦታ እንዲይዙ ማድረግ ነው፡፡በመጻኢ እድላችን ላይ ስልጣን ሲኖረን ልጆቻችንም ያብባሉ ፡፡በሁለት አለም መካከል ይጓዛሉ ባህላቸውም ለአገራችው የሚያበረክቱት ስጦታ ይሆናል ፡፡ ህገ መንገስቱንም የመጀምሪያው ህዝቦች ድምጽ ሰፍኖበታል ብለን እንጠራዋለን  ፡፡

ማካራታ የአጀንዳችን ፍጻሜ ነው ፡፡ከትግል በኋላ በአንድ ላይ መሆን ፡፡ ከአውስትራሊያ ህዝብ ጋር ፍትሃዊ እና እውነተና ግንኙነት የመፍጠር ምኞታችንን የሚያቅፍ፤ እንዲሁም የተሻለ ነገን ለልጆቻችን በፍትህ እና የራስን እድል በራስ መወሰንን የሚያረጋገጥ ህገ መንግስት እንሻላል ፡፡  በመንግስት እና በቀደምት ብሄሮች ታሪክ ዙሪያ የሚነገሩ እውነቶችን በተመለከተ የማካራታ ኮሚሽን ሂደቶቹን በመከታተል ስምምነት እንዲያደርድ እንፈልጋለን ።

በ1967 ተቆጥረናል ፤ በ2017 እንድንደመጥ እንፈልጋለን ፡፡ የምንኖረው ካምፕን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው ፡፡ ነገር ግን በመላው አገሪቱ መሰራጨት ጀምረናል፡፡የአውስትራሊያውያ ነገ የተሻለ እንዲሆን እናንትንም አብራችሁን እንድትጓዙ እንጋብዛችኋለን፡፡  

 

ለተጨማሪ መረጃ  የኡሉሩን መግለጫን የያዘውን ድረ-ገጽ  ይጎብኙ ፤ ወይም የነባር ዜጎች የህግ ማእከልን በኢሜል   ያግኙ ።

ከ20 በላይ የአቦርጂናል ቋንቋዎችን ማለትም (ከሰሜናዊ ግዛት እንዲሁም ከደቡብ እና ምእራብ አውስትራሊያ የማህበረሰብ ክፍሎችን ) ያካተተ ሲሆን ፤ የመጀምሪያዎች ዜጎች ቋንቋዎች በተተረጎሙ መጠን ቁጥሩ የሚጨምር ይሆናል ።እንዲሁም ይህ ስብስብ  ከ 60 በላይ በአውስትራሊያ በባህል እና በቋንቋ ዝንቅ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቋንቋ አካቷል።


Share