Settlement Guide: free English classes for migrants

የጎልማሳ መጤ እንግሊዝኛ ፕሮግራም (AMEP) ትልቁ የሠፈራ ፕሮግራም ሲሆን፤ ለአዲስ መጤዎች ከ500 ሰዓታት በላይ የእንግሊዝኛ ቁንቋ ትምህርትን ይሰጣል።

Settlement Guide: 5 facts on AMEP

Ramani na watu wanao ishi nchini Australia Source: Getty Images

፩ ቋሚና የተወሰኑ ጊዚያዊ ቪዛ ያላቸው የቅርብ ጊዜ መጤዎች የነጻ ትምህርት ለማግኘት መመዘኛውን ያሟላሉ።

AMEP ለሁሉም ቋሚ ቪዛ ላላቸውና በተጨማሪም ለተወሰኑ ጊዛያዊ የመቆያ ቪዛ ያላቸው ሆኖ ለመግባባኢያ ደረጃ የሚያደርስ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ደረጃ ክህሎት ለሌላቸው በነጻ ያስተምራል።

Australian visa
Source: SBS

፪ ለፕሮግራሙ ብቁ የሆኑ ቪዛ ያላቸው አውስትራሊያ ውስጥ በዘለቁ ስድስት ወራት ውስጥ AMEP ዘንድ ቀርበው ሊመዘገቡ ይገባቸዋል።

ዕድሜያቸው ከ18 ዓመታት በታች የሆኑ ለመመዝገብ የተራዘመ ጌዜ ይኖራቸዋል። ሁሉም ተማሪዎች የትምህርት ፕሮግራማቸውን በአምስት ዓመታት ውስጥ የግድ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል።

New arrivals

፫ ኮርሶቹ በአገር አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያለው በእንግሊዝኛ የመናገርና መጻፍ የምስክር ወረቀት አካል ናቸው።

ከጀማሪዎች እስከ አማካይ ደረጃ አራት የጥናት ደረጃዎች አሉ።

Accredited courses

፬ በተለያዩ ሥፍራዎች ለመማር በርካታ መንገዶች አሉ። በትምህርት ክፍለ ጊዜያት በአካል ተገኝቶ ሙሉ ቀን፣ ግማሽ ቀን ወይም በተልዕኮ ትምህርት፤ በኢንተርኔት ወይም ቤት ድረስ መጥተው በሚያስተምሩ መምህራን በመላው አውስትራሊያ 250 ሥፍራዎች ውስጥ በሚገኙ የምዝገባ ፈቃድ ካላቸው ግልጋሎት ሰጪዎች ዘንድ መማር ይቻላል።

Classroom

፭ ዕድሜያቸው ለትምህርት ያልደረሱ ህጻናት ላሏቸው ተማሪዎች ነጻ የሙዋዕለ ሕጻናት ክብካቤ ይሰጣል።

የAMEP ግልጋሎት ሰጪዎች ዕድሜያቸው ለትምህርት ቤት ያልደረሱ ህጻናት ኖሯቸው ትምህርት እየተከታተሉ ላሉ ተማሪዎቻቸው ነጻ የሙዋዕለ ሕጻናት ክብካቤን የማሰናዳት ኃላፊነት አለባቸው።

Childcare
Source: AAP

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በ26 ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ያለውን Adult Migrant English Program ይጎብኙ።

ወይም ስለ ኮርሶቻቸው ተጨማሪ መረጃን ካሹ AMES Australiaን በ13 26 37 ደውለው ያግኙ።

 


Share
1 min read
Published 9 September 2016 2:52pm
By Ildiko Dauda
Presented by Kassahun Seboqa
Source: AMEP

Share this with family and friends