ነባር ዜጎች ከመሬታቸው ጋር ያላቸውን ጥልቅ ቁርኝቶች መረዳት

Single hand of a Young Indigenous girl on the rocks

Understanding the profound connections First Nations have with the land. Vick Smith/Getty Images Source: Moment RF / Vicki Smith/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች መሬት ጥልቅ መንፈሳዊ ፋይዳን የያዘ፣ ከማንነታቸው፣ ውሁድነትና የአኗኗር ዘዬ ጋር ተጋምዶ የተቆራኘ ነው።


አንኳሮች
  • መሬት ለነባር ዜጎች ማንነታቸውና ተዋሃጅነታቸው የታነፀበት የማይነጠል አካል ነው
  • የቁርኝት ግንዱ ለትውልዶች በታሪኮች የተወራረሰ ነው
  • የተቀደሱ ሥፍራዎችን ስለ ቅዱስ ሥፍራዎች ዕውቀትን የጨበጡና ያላቸውንም ልዩ ትርጓሜ የተርዱ ብቻ መሆን አላባቸውንም
የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ከተለዋዋጭ ገፀ ምድረ ጋር ራሳቸውን እያዋደዱ አውስትራሊያን ቢያንስ ለ 60,000 ዓመታት ኖረውባታል።

የዩን ብሔር ዋላባንጋዋ ሴት አክስት ዴይድሬ፤ የተከበሩ አረጋዊት፣ ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ብሔራዊ ፓርኮችና የዱር እንሰሳት አገልግሎት ጋር የሚሠሩ የግኝት ባለ አደራ ናቸው።

ለአክስት ዴይድሬ፤ መሬት በባለቤትነት የሚያዝ ንብረት ሳይሆን ክብካቤንና ከበሬታን የሚሻና ከእሳቸው የማይነጠል አካል ነው።
መቼውንም ቢሆን መሬትን በባለቤትነት አንይዝም፤ ባለቤትም አንሆንም። ለመሬት ጥበቃ የማድረግ ሚና አለን። የአገራችን ምድር ከሚቸረን ውስጥ ውኃና መጠለያ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው።
አክስት ዴይድሬ ማርቲን
“መሬት ቃል ነው፤ ሆኖም በደም ስራችን ውስጥ ተመላላሽ ነው። የመጀመሪያ እስትንፋሳችን እንደሆነ ሁሉ፤ የመጨረሻችንም ይሆናል“ ብለዋል።
Aunty Deidre Martin.jpg
Aunty Deidre Martin is an Aboriginal discovery ranger. Credit: Aunty Deidre Martin.
አክስት ዴይድሬ ማርቲን ከመሬታቸው ጋር ያላቸው ጥብቅ ትስስሮሽ የቁርኝት ስሜትን ለመቀስቀስ በቂ ስለመሆኑ ይናገራሉ።

“ከሲድኒ ወደ አገር ቤት ስጓዝ፤ ልክ ኪያማ መታጠፊያ ላይ ደርሼ የባሕር ዳርቻውን ስመለከት፤ የቁርኝት ስሜቱ አሸንፎኛል፤ እናም... ቀዬዬ ነኝ ብዬ አስባለሁ” ሲሉም አክለዋል።

ዴስሞንድ ካምፕቤል፤ በሰሜናዊ ግዛት ኩሩ የጉሪንጂ እና ኤላዋ ንጋላካን ሰው ናቸው። እሳቸውም ወደ ቀዬያቸው ሲመለሱ ተመሳሳይ ስሜት እንዳደረባቸው ገልጠዋል።

አሁን ነዋሪነታቸው ሲድኒ የሆነው የ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቀዬአቸው ውስጥ ስለመገኘት ሲያስቡ ሰውነታቸውን የመውረር ስሜት እንደሚሰማቸው ይናገራሉ።

“ምንም እንኳ በዘላቂነት እዚያ ያላደግን ቢሆንም፤ ልክ ትናንት እዚያ የነበርን ያህል ሆኖ ይሰማናል። አይረሴ ነው። የደህንነት ስሜት ያሳድራል። እንደ ነባር ዜጋ ሰው እዚያ መሆን ያለብን የሆነ ዓይነት ስሜት ያሳድራል” ሲሉ።

አቶ ካምፕቤል፤ ከቀያቸው ርቀው ያሉ ቢሆንም እንኳ ቁርኝታቸው የፀና ነው፤ ወደ ቅድመ አያቶቻቸው መሬት አዘውትሮ የመመላለሱ ፋይዳ ለባሕልና ቋንቋ ትግበራ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ መንፈሳዊ ቁርኝነትም ጭምር ማጎልበት እንደሁ አበክረው ያስረዳሉ።

“ሙሉዕ ያደርገኛል፤ መንፈሴን ይመላዋል። ሲድኒን የመሰለ ሥፍራ እንድኖርና 'እንኳን ወደ አገር ደህና መጡ' ለመሰለ ድርጅት እንድሠራም ያስችለኛል... ተአማኒነትን ተላብሼ፤ ባሕልና ቋንቋዬን ጠብቄ እንዳቆይ ግድ ይለኛል። ያንን ማድረግ የምችለው ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ቀዬዬ በመመላለስ ብቻ ነው” ብለዋል።
Desmond_bio photo.JPG
CEO of Welcome to Country, Desmond Campbell. Credit: Desmond Campbell.

መሬትን የተመለከቱ ታሪኮች

አቶ ካምፕቤል የቁርኝት ምንጮች በታሪክ ለትውልዶች መተላለፋቸውን ያስረዳሉ።

ታሪኮች፣ መንፈሶችና ቁርኝቶች እንደ መጡበት ምድር ይለያያል ሲሉም ያክላሉ።

“የእኔ ጉሪንጂ ወገን፤ ማለትም የአባቴ ወገን፤ የበረሃ አገር ነው። እንሰሳቱ የተለዩ ናቸው፤ የአየር ንብረት ወቅቶቹ የተለዩ ናቸው፤ [በእናቴ ወገን] እንዲሁ ወጎቹ የተለዩ ናቸው” ይላሉ።

አቶ ካምፕቤል፤ ስለ መሬት የሚነገሩት ወጎች በዕውቀትና ትምህርቶች የተጋመዱ ናቸው። ልክ መቼና እንዴት ማደን እንደሚገባና አግባብ ባልሆነ የአየር ንብረት ወቅት በእሳት መጫወት የሚያስከቱሉትን መዘዞች አካታች እንደሆኑ ይናገራሉ።
ብራድሊ ሃዲ፤ ኩሩ የንጌማ ኡዋላሪ፣ ኮማና ካሚላሮይ ሰውና ባርዎን ወንዝ አጠገብ የሚገኘው የዘመናዊው ባለ አደራ ናቸው።

ወንዝን "ደም እና መለያ" ሲሉ ይገልጣሉ።

አቶ ሃዲ እንደ አስጎብኚ ሠራተኛነታቸው ስለ መሬት ወጎችንና ታሪኮችን ያስረዳሉ።

ለቀጣዩ ትውልድ ለማሳለፍ ወጎችን በማውጋት የግድ እንዲቆዩ ማድረግ እንዳለባቸው ይናገራሉ።

“ጉብኝቱ እኔን የተመለከተ ሆኖ አያውቅም፤ ይሁንና የእኔን አረጋውያን ክብር ለመቸር፤ ለወጣቶች በማጋራት ታሪክን ለዓለም ማጋራቱን እንዲቀጥሉበት መድረክ ማመቻቸት ነው፤ ያንንም ማድረግ የእኛ ተግባር ነው” ብለዋል።
Copy of Untitled Design.png
Bradley Hardy and Brewarrina Aboriginal Fishing Traps. Credit: Bradley Hardy.

ቅዱስ ሥፍራን መገንዘብ

የብሪዋሪና አቦርጂናል የአሣ ወጥመዶች በዓለም ካሉ ጥንታዊ ሰብዓዊ ግንባታዎች አንዱ ነው። በ U እና C ስትራቴጂካዊ ቅርፆች የቆሙ አለቶች ናቸው፤ ለመንጋና አሣ ጠመዳ ብቻ ሳይሆን የተወሰኑ አሣዎች እየተዘዋወሩ የሕይወት ጊዜያቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችልም እንደሁ ያስረዳሉ።

እንዲሁም በርካታ ጎሳዎች አንድ ላይ የሚሰባሰቡበትም ነው።
ቅዱስ ሥፍራ ስለሆነ፤ ሙከራና ጥበቃ ማድረግ አለብን። በአብዛኛው ለእኛ ሰዎች የሚሆን ነው። የእኛ ዋነኛ ተግባር ስለ እነሱ ለሰዎች አለመናገር ብቻ ሳይሆን ወጣቶቻችንንም ማሳተፍ ጭምር ነው፤ ሆኖም ለዓለም እኒህ ልዩ ሥፍራዎች መሆናቸውን [ማሳወቅ] አለብን።
ብራድሊ ሃዲ
አክስት ዴይድሬም እንዲሁ የተቀደሱ ሥፍራዎችን ከመጎብኘት በፊት ጠቀሜታቸውና ፋይዳዎቻቸውን ማወቅ እንደሚገባ ያመላክታሉ።

“ዕውቀት የተከማቸባቸው ሥፍራዎች ስለሆኑ፤ በቂ ዕውቀት እስኪኖርዎት ድረስ ሊጎበኙዋቸው አይችሉም፤ ለምሳሌ ያህልም በወንዶችና ሴቶች የማይደረሱ የመሰሉ ሥፍራዎችን” ይላሉ።
First nation Australian aboriginal people using spears to hunt seafood in Cape York Queensland Australia
Silhouette image of First Nation Australian aboriginal people, father and son, going to hunt seafood in Cape York, Queensland, Australia. Credit: Rafael Ben-Ari/Getty Images Credit: Rafael Ben-Ari/Getty Images
ለነባር ዜጎች ቅዱስ ሥፍራዎች እንደ ብሔር ዝንቅነታቸው ፋይዳዎቻቸው በጣሙን ይለያያሉ። የተወሰኑ ሥፍራዎች የአምልኮ ሥርዓቶች ወይም ፋይዳዎች ታክለውባቸው በወንዶችና ሴቶች የማይደረሱ የተቀደሱ ሥፍራዎች ሆነው ሳለ፤ ሌሎች ለተወሰነ ፆታ ብቻ ይሆናሉ በማለት ያስረዳሉ። .

አክስት ዴይድሬ ስለ ቅዱስ ሥፍራዎች ለማኅበረሰቡ ማስተማር የእሳቸው ኃላፊነት እንደሆነና ዕውቀታቸውን ለጎብኚዎች ማካፈሉንም እንደሚደሰቱበት ይገልጣሉ።

የነባር ዜጎች መሬትን በጥልቀት መዝለቅና ፋይዳዎቿቸውንም መገንዘብ የዕውቀት ሃብትን ገልጦ ሊያሳይ ይችላል። ይሁንና የነባር ዜጎች ቅዱስ ሥፍራዎች ዘንድ ሲደርሱ ከበሬታን መቸርን ከአካባቢው የነባር ዜጎች ማኅበረሰባት ወይም የመሬት ምክር ቤቶች መመሪያን ሊጠይቁ ይገባል።

አቶ ሃዲ “የአሣ ወጥመዶችም ይሁን ወይም የሌላ ሥፍራ ታሪኮች፤ ሰዎች ወደ እዚያ ዘለቀው የእኛን እውነተኛ ታሪክ እንዲያውቁ እንሻለን። ሰዎች መጥተው ስለ እነዚህ ጉዳዮች እንዲማሩ፤ እንዲሁም ቁሶቻችንን ልብ እንዲሉና ከበሬታም እንዲቸሯቸው እንወዳለን” ብለዋል።

Share